
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራልን ጎበኙ።
ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ ነው። ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር ጅማ ቤተመንግሥት እና በርካታ ቅርሶች ድረስ አቻ የማይገኝለት የታሪክ እና የባሕል ሀብት እንዳላት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገራችን የቅርስ ጥበቃ እና እድሳትን ቅድሚያ የምትሰጥበት በርካታ ፀጋ አላት።
ቱሪዝምን ማስፋፋት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቁልፍ የትኩረት መስክ በመኾን በኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ከአምስቱ ምሰሶዎች አንዱ ኾኖ እየተሠራበት ይገኛል።
ከአለም አቀፍ ምርጥ ተመክሮ በመማር ኢትዮጵያ የባሕል ሀብት ቅርሶቿን የመጠበቅ እና ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ልማት ሥራ ጥረቷን ለማጠናከር ትችላለች በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስፍሯል።