ከፍተኛ መሪዎች ከጢስ ዓባይ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።

16

ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች በወቅታዊ የሰላም እና ልማት ሥራዎች ዙሪያ ከጢስ ዓባይ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።

ውይይቱ የባለዘንባባዋ ባሕር ዳር ከተማ አንዱ የቱሪዝም ማዕከል የኾነችው ጢስ ዓባይ ከተማ ሰላሟ ተጠብቆ ማኅበረሰቡ በሙሉ አቅሙ እንዲያለማ ለማስቻል ያለመ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የመጀመሪያው ክልላዊ ራዲዮ”
Next article3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልል መድረሱን ግብርና ቢሮ አስታወቀ።