
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር “ትውልድ በመምህር ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል ከዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደ ወይን (ዶ.ር) በዕውቀት በክህሎት እና በአመለካከት የዳበረ ትውልድ የሚያፈራው የትምህርት ዘርፍ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የሚደረጉ ውይይቶች በሀገር እድገትና ሰላም ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ግርማይ ልጅዓለም በፖለቲካው፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚው የተገኙ እምርታዊ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንዲሁም የቀጣይ የመፋትሔ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኝ በትምህርት ሴክተሩ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ለተወያዮች አቅርበዋል።
በውይይቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መስፍን አበጀ (ዶ.ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እና ሌሎችምየዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
