“ትምህርት የዘላቂ ሰላምና የሁለንተናዊ እድገት መሠረት ነው” አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ

25

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍሰሃ ደሳለኝ እና ሌሎች የክልልና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ከወልድያ ዩንቨርሲቲ መምህራን ጋር “ትውልድ በመምህር ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ መልእክት እየተወያዩ ነዉ።

በውይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍሰሃ ደሳለኝ “ትምህርት የዘላቂ ሰላምና የሁለንተናዊ እድገት መሠረት ነው” ብለዋል። አቶ ፍሰሃ መምህራን ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ትውልድን በመቅረጽ ረገድ የማይተካ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በትምህርት ልማት ዘርፍ አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ተወዳዳሪ ዜጎችን በመፍጠር በኩልም አይነተኛ ለውጥ መምጣቱን ገልፀዋል። በሀገረ መንግሥትና በአወንታዊ ሰላም ግንባታ ሂደት ምሁራን የላቀ ድርሻ አላቸው ያሉት አቶ ፍሰሃ የሰላም እጦት መንስኤዎችንና መፍትሔዎቹን በማመላከት በዘላቂነት ለመፍታት የምርምር ሥራዎችን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

የወልድያ ዩንቨርሲት ፕሬዝዳንት አበበ ግርማ (ዶ.ር) እንደገለፁት የትምህርት ዘርፉ ለሀገር እድገት የሚያበረክተው አስተዎፅኦ ከፍተኛ ነው። ለሀገር ዘብ የሚቆም በመልካም ግብረገብነት የታነፀና በእውቀት የበለፀገ ዜጋ እንደሆነም አሥረድተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአስተሳሰብ የለማ ትውልድን ለመቅረፅ የጎላ ፋይዳ አላቸው” የደሴ ከተማ አሥተዳደር
Next articleመምህራን ሀገር ያለችበትን ችግር በመረዳት ገዥ ሀሳቦችን የማቅረብ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተናገሩ።