
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከጤና ቢሮ፣ ከአማራ ክልል የአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የመንቀሳቀስ ጉዳት ያለባቸውን ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔውን በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
በጉባዔው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ንጹህ ሽፈራው አካል ጉዳተኞች በማኅበር ተደራጅተው በመሥራት፣ ተጽዕኖ በመፍጠር እና ተደማጭ ለመኾን ያስችለዋል ብለዋል። በመንግሥት የወጡ መመሪያዎች፣ አዋጆች እና ደንቦች በሥራ መተግበር የሚቻለውም በማኅበር ታቅፎ ሲሠራ እንደኾነ ወይዘሮ ንጹህ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፍሬሰላም ዘገየ በክልሉ ከአራት ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች አሉ ነው ያሉት። ለእነዚህ አካል ጉዳተኞችም ዘርፈ ብዙ ምቹ ኹኔታዎች እንዲፈጠርላቸው እና የወጡ ሕጎች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ ለማድረግ ማኅበሩ እየሠራ መኾኑን ተጠቁሟል።
የመንቀሳቀስ ጉዳት ያለባቸው ማኅበር የ2017 በጀት ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ እየገመገመ ይገኛል።
ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን