ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ።

12

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ፈረንሳይ ገብቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እና ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

የሁለቱ መሪዎች ውይይት መጠነ ሰፊ ርዕይ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገ እና አስደሳች እንደነበርም ጠቁመዋል። ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል እና በታኅሳስ ወር በአዲስ አበባ ከነበረን ውይይት ቀጥለን ስላካሄድነው ፍሬያማ ውይይት ምስጋናዬን አቀርባለሁም ነው ያሉት።

የሁለቱ ሀገራት ትብብር በብዙ ጠቃሚ ዘርፎች የቀጠለ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንግድ ትስስሮቻችንን የበለጠ ማሳደግ ከቅድሚያ የትኩረት ማዕከሎቻችን አንዱ ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝቦች ጥቃት እየተፈጸመባቸው ያሉት በራሳቸው ሰዎች መኾኑ ያሳዝናል።
Next articleአካል ጉዳተኞች ምቹ ኹኔታዎች እንዲፈጠርላቸው እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን አስታወቀ።