ፋይዳ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመሥጠት እና ፍትሐዊ አሠራርን ለመዘርጋት እንደሚያግዝ የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ አስታወቀ።

17

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለሠራተኞች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ መርሐ ግብር አካሂዷል።

የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ጥላሁን ሽመልስ ቢሮው በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎትን ለመስጠት ሢሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።

አሁን ላይም ሠራተኞች እንደ ሀገር እየተተገበረ የሚገኘውን የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲኾኑ መደረጉን ገልጸዋል።

ፋይዳ መታወቂያ ዜጎች ወጥ ማንነት እንዲኖራቸው፣ ዲጂታል አሠራርን በመዘርጋት የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መኾኑን ነው የገለጹት። የሚታዩ ብልሹ አሠራሮችን ለማረም እና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ አቅም ይኾናል ብለዋል።

የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ሠራተኛ ዓባይነሽ አሰፋ የፋይዳ መታወቂያን ሀገራዊ ጠቀሜታ በመረዳት ቀድመው ተጠቃሚ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ተገቢውን አገልግሎት ለማግኘት እና አሠራርን ለማዘመን ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመኾኑ ሁሉም ዜጋ መታወቂያውን ቢያወጣ ተጠቃሚ እንደሚኾንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሰላምን በዘላቂነት ለመገንባት የዩንቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ሚና ከፍተኛ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleየፈተና ውጤት ማሳወቅ፦