“ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

12

ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል ነው ያሉት።

ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ እየተመራን እጅግ አስፈላጊ ውሳኔ ወስነናል። ይህም ዘመናዊ፣ አካታች፣ መሠረት ያለው እና ሊሰፋ የሚችል ዲጂታል የማንነት ሥርዓት መገንባት ነው።

ይሄንንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ይሄንን ሥርዓት ‘ፋይዳ’ ብለን እንጠራዋለን። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሀገራችን ካሉ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት ስብራቶች ውስጥ አንዱ ብልሹ አሠራር ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next article“ፍርድ ቤቶች የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብት በማረጋገጥ ረገድ የመጨረሻ አማራጮች ናቸው” አቶ ዓለምአንተ አግደው