የንግዱ ማኅበረሰብ ምርትን በፍትሐዊነት በማቅረብ ማኅበራዊ ኀላፊነትን እንዲወጣ ተጠየቀ።

9

ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር እየተወያየ ነው። በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ብርሃን ንጉሴ ለአንድ ሀገር እድገት እና ዘላቂ ሰላም መስፈን የንግዱ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ምርት እና አገልግሎትን ለመሸጥ የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም መገንባት ይገባልም ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ማንኛውም ወደ ንግድ ሥራ የሚሠማራ አካል ሕግን አክብሮ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ምክትል ኀላፊ ገነት አሰፋ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል። ምርት እና ምርታማነትን መጨመር፣ ሰፋፊ የሥራ ዕድል መፍጠር እና በፍትሐዊነት ላይ የተመሠረተ የግብይት ሥርዓት ማስፈን ከንግዱ ማኅበረሰብ ይጠበቃል ነው ያሉት።

የንግዱ ማኅበረሰብ የሚቀርቡ ምርቶችን በፍትሐዊነት ለማኅበረሰቡ በማቅረብ ማኅበራዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕጻናት መብታቸው እስከ ምን ድረስ ነው?
Next article“በሀገራችን ካሉ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት ስብራቶች ውስጥ አንዱ ብልሹ አሠራር ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ