
ደሴ: ግንቦት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በመክፈቻ ንግግራቸው የክልሉን ሰላም እና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳደሩ በተለይ የቀበሌን ችግር ማዕከል ያደረገ ውይይት በማድረግ፣ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በመሥራት እንዲሁም የጸጥታ መዋቅሩን አደረጃጀት በማጠናከር ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት።
ምክትል ርእሰ መሥተዳደሩ በመድረኩ የክልሉን ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አሥተዳደር እና የልማት ሥራዎችን በመገምገም በቀጣይ በትኩረት የሚሠሩ ሥራዎችን አቅጣጫ እናስቀምጣለን ብለዋል፡፡
በውይይቱ በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች፣ የጸጥታ አባላት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
ዘጋቢ፦አንተነህ ፀጋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን