የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄዎች ለመመለስ እየሠራ መኾኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር አስታወቀ።

20

ጎንደር: ግንቦት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ከጤና ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊ የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሕጋዊ መንገድ እንዲፈፀምላቸው ጠይቀዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ማኅበረሰቡን እያገለገሉ ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱ እንደሚሠሩም ነው የተናገሩት።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ ገበያው አሻግሬ የጤና ባለሙያዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገራዊ ሪፎርም እየተሠራ መኾኑን ባቀረቡት ሰነድ አመላክተዋል።

ኀላፊው በጤና ባለሙያዎች የተነሱ ጥያቄዎች እንዲፈቱ ሲጠይቁ ባለሙያው የሚጠበቅበትን ሙያዊ ግዴታ በመወጣት ማኅበረሰቡን ማገልገል እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።

በውይይቱ የተገኙት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ የዞኑ አቅም በፈቀደ መጠን የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄዎች ለመመለስ እንሠራለን ብለዋል።

ይሁን እንጅ ከዞኑ አቅም በላይ የኾኑ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች ለሚመለከተው አካል በማድረስ እንዲፈታ ይደረጋል ነው ያሉት ዋና አሥተዳዳሪው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleተማሪዎች አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን በዕቅድ እንዲሠሩ በመደረጉ ውጤት ተገኝቷል።
Next article“የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየተሠራ ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው