የኢቢሲ የሚዲያ ቴክኖሎጅ መሪዎች እና ባለሙያዎች በአሚኮ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

30

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ግዙፍ እና ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ የቀጥታ ሥርጭት ማስተላለፊያ ስቱዲዮ (ኦቢቫን) አስገንብቶ ማስገባቱ ይታወሳል። ይህ የሚዲያ ቴክኖሎጂ የላቀ የመገናኛ ብዙኅን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ቴክኖሎጅ ባለሙያዎች እና መሪዎች በባሕር ዳር የአሚኮ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው ይህንን ቴክኖሎጅ ተመልክተዋል። በምልከታው ላይ ከኢቢሲ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና መሪዎች በተጨማሪ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ (ቢኬጂ) የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሰጠኝ እንግዳው ተገኝተዋል።


ጉብኝቱ ይህንን ግዙፍ የሚዲያ ቴክኖልጂ በሀገር ውስጥ አቅም ለመገንባት ይቻል እንደኾነ አይቶ ለመገምገም፤ ሠርቶም ሌሎች ሚዲያዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው። የሚዲያ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ዋናውን የአሚኮ መሥሪያ ቤት ግቢ እና የሥራ እንቅስቃሴውንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሀገር በመገንባት ረገድ የጤና ባለሙያዎች ድርሻ ከፍተኛ ነው።
Next articleተማሪዎች አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን በዕቅድ እንዲሠሩ በመደረጉ ውጤት ተገኝቷል።