“ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

32

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል መሪ መልዕክት እየተካሄደ ባለው ኤክስፖ ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሐ ግብር አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጠተው አንሰተዋል።

ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መኾኑን አውስተዋል። እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ፣ “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” አይነት ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞችን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች ነው ያሉት።

በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት ማንሳታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተሟላ የሕዝብን ደኅንነትን ለማረጋገጥ ማኅበረሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ።
Next articleሀገር በመገንባት ረገድ የጤና ባለሙያዎች ድርሻ ከፍተኛ ነው።