የተሟላ የሕዝብን ደኅንነትን ለማረጋገጥ ማኅበረሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ።

12

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በከተማ አሥተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የተሠሩ ሥራዎች ለምክር ቤት አባላት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አዲስ ትርፌ ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በተሠራው ሥራ የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል።
በመንግሥት ብቻ የተሟላ ሰላምን ማረጋገጥ እንደማይቻል ያነሱት ምክትል አፈ ጉባኤዋ የተሟላ የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥ የተጀመረው የማኅበረሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ልጆች በሀገራቸው ባሕል፣ ወገ እና እሴት ተቃኝተው እንዲያድጉ ከቤተሰብ ጀምሮ ግብረ ገብነትን ማስተማር እንደሚገባም ነው የገለጹት። ለሀገር ዕድገት መሠረት የኾኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲቀስሙ መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ዋጋ የሚጨምሩ፣ የሚመረቱ ምርቶችን ወደ ከተማዋ እንዳይገባ የሚሠሩ ቡድኖችን መታገል እንደሚገባም አንስተዋል።
ባሕር ዳር ከተማ ደኅንነቷ የተጠበቀ፣ ለኗሪዎች እና ለጎብኝዎች ምቹ እንድትኾንም እየተሠራ ያለውን ሥራ ማኅበረቡ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የከተማዋ ሰላም መኾን ውጤቶች እንደኾኑ ተገለጸ።
Next article“ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)