“የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመልሰው የልማት አቅም እንዲኾኑ የክልሉ መንግሥት ድጋፋን አጠናክሮ ይቀጥላል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

62

የታጠቁ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመልሰው የልማት አቅም እንዲኾኑ አጋር አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ። ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚያስችልበት ዙሪያ ከክልሉ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ምክክር አድርጓል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን የተሐድሶ ሥልጠና በመስጠት እና መልሶ በማቋቋም ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል። የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ እና በመላ ሀገሪቱ ሰላም እና ደኅንነትን የማረጋገጥ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል ነው ያሉት።

በግጭት ወቅት በሁለቱ ተፋላሚ ኀይሎች ብቻ ሳይኾን በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳት የሚያስከትል መኾኑን በመረዳት የታጠቁ ኀይሎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። ወደ ሰላም የገቡ ታጣቂ ኀይሎችን ደግሞ የክልሉ መንግሥት ከብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተሐድሶ ሥልጠና በመሥጠት ወደ ተሟላ ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖሩ መደረጉን ገልጸዋል።

አሁን ላይም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከሚገኙ የታጠቁ ኀይሎች ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። በቀጣይ የተሐድሶ ሥልጠናውን ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ብለዋል። የታጠቁ ኀይሎችን ወደ ሰላማዊ ኑሮ ተመልሰው የልማት አቅም እንዲኾኑ ኮሚሽኑ በሚያደርገው ጥረት የክልሉ መንግሥት ድጋፋን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። አጋር አካላትም ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የቀድሞ ታጣቂዎችን በማሠልጠን እና መልሶ በማቋቋም ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል። ለዚህም የመንግሥት መዋቅር ለኮሚሽኑ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለጋሽ ሀገራትን በመወከል የተገኙት ባዝል ማሰይ ለኮሚሽኑ የሚደረገው ድጋፍ በማስቀጠል ለሰላም እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የፋይናንስ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ የፋይናንስ ተቋማት በትብብር መሥራት እና ዘርፉን ማዘመን ይገባቸዋል” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleየኪነ ጥበብን አቅም ለሀገር ግንባታ ለመጠቀም እየተሠራ ነው።