የማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እውነትን ለሕዝብ በመንገር ሀገራዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

17

ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር “በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ቀጣይ አቅጣጫ” በሚል መሪ መልዕክት ከማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና ከኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በባሕር ዳር ከተማ ውይይት እያደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በክልሉ የገጠመው ገጭት የመጨረሻ መፍቻ ቁልፉ ጦርነት ሳይኾን ምክክር እና ውይይት ነው ብለዋል። ለዚህም የሰሜኑን ጦርነት በማሳያነት አንስተዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እውነትን ለሕዝብ በመንገር ሀገራዊ ሚናቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። የማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሀገርን በማረጋጋት ረገድ የበኩላቸውን እንዲሠሩም አሳስበዋል።

ሕዝብ የሚያሸብረውን፣ ያልተደረገውን እንደተደረገ ሐሰት የሚነዛውን ኀይል ማሸነፍ የሚቻለው የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያው ሙያዊ ግዴታውን በመወጣት እውነትን ለሕዝብ መንገር ሲችል እንደኾነም አንስተዋል።

ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየሕዝቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እየተሠራ መኾኑን የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።
Next article“የፋይናንስ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ የፋይናንስ ተቋማት በትብብር መሥራት እና ዘርፉን ማዘመን ይገባቸዋል” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ