
ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማዕከሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሲኾን የማንኛውንም በሽታ አምጪ ተህዋስ ምንነት መለየት የሚያስችል ነው።
በመኾኑም አዲስ በሽታ ሲከሰት ተህዋሱን ለይቶ አስፈላጊውን የመከላከል እና የማከም እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ፣ የአማራ ክልል የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ እና በአማራ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዋና ጸሐፊ ታፈረ መላኩን (ዶ.ር) ጨምሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የአጋር አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን