
ደብረታቦር: ግንቦት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቀደመ ባሕልን በመጠቀም ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ በደቡብ ጎንደር ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል። በደቡብ ጎንደር ዞን “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በውስጥ ያሉ ችግሮችን በመፍታት የቀደመ ባሕልን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ መንበር ክፈተው በተሳሳተ መንገድ አላስፋላጊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላትን የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲመክሩ እና እንዲመልሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አማረ ሰጤ ከመገዳደል የሚገኝ ትርፍ አለመኖሩን ተናግረዋል። ችግሩን በምክክር መፍታት እንደሚገባም ገልጸዋል። “እየተጎዳ ያለው ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ እና አርሶ አደሩ ነው” ያሉት ምክትል አፈጉባኤው ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ዓለምነሽ ንጉሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን