የፌደራል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በዘጠንኛው የመላ አማራ ጨዋታ ለመታደም ኮምቦልቻ ገቡ።

58

ደሴ: ግንቦት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ልዑክ ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል።

ልዑኩ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳን ጨምሮ የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በደሴ ከተማ አዘጋጅነት በሚካሄደው ዘጠነኛው የመላ አማራ ጨዋታ ላይ ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራን ሕዝብ ለማጎሳቆል የተነሱ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን አምርሮ መታገል ይገባል።
Next articleየባሕር ዳር ከተማ የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት የመብራት ሥራ ተጠናቅቋል።