“ከጥፋት መክሮ መመለስ የሃይማኖት አባቶች ተቀዳሚ ተግባር መኾን አለበት” የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም

20

ደሴ: ግንቦት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ አሥተዳደር በከተማዋ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎች እና የእድር መሪዎች ጋር “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት ውይይት ተካሂዷል።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ሰላም ለሁሉ ነገር መሠረት ነው ብለዋል።

አቶ ሳሙኤል አክለውም እምነታችንን ብቻ ታሳቢ አድርገን ሳይኾን ቅድሚያ ሰው መኾንን ብቻ አስቀድመን ልንሠራ ይገባል ብለዋል። የአንዳችን ሰላም ማጣት የሌላችን ሰላም ማጣት መኾኑን ልንረዳ ይገባል ነው ያሉት።

እንደ ደሴ ከተማ ያለንን ሰላም ከልማት ሥራችን ጋር አስተሳስረን መጓዝ ይኖርብናልም ብለዋል።

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም ስለ ሰላም እጦቱ ከመናገር ባሻገር ሰላም የሚረጋገጥበት መፍተሄ ላይ አብሮ መሥራት ከሃይማናት አባቶች ይጠበቃል ብለዋል። ከጥፋት መክሮ መመለስ የሃይማኖት አባቶች ተቀዳሚ ተግባር መኾን አለበት ያሉት ቢሮ ኀላፊው፤ በምክር መመለስ ያልቻሉ ኀይሎች ሊወገዙ ይገባልም ብለዋል።

በየትኛውም ዓለም ላይ ጦርነት እና ግጭት ሰላም አምጥቶ አያውቅም ያሉት አቶ ብርሃኑ ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ የሃይማኖት አባቶች ሚና የጎላ መኾኑን አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንደየ እምነት ተቋማቸው ምእመናን ስለ ሰላም ዋጋ እንዲገነዘቡ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ መኾናቸውን ገልፀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“እንደ ሕዝብ ከልብ በመነጨ ኀላፊነት መነጋገር እና ማሰብ ይጠበቅብናል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next article“ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተኪ ምርቶችን በማምረት የኢትዮጵያ ብልጽግና ማሳያዎች ናቸው” አቶ አደም ፋራህ