ኅብረተሰቡ ጽንፈኝነትን በጽናት ሊያወግዘው እንደሚገባ ተገለጸ።

14

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ውይይቱ ከቀበሌ ጀምሮ እየተካሄደ መኾኑን ገልጸዋል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የጥፋት ቡድኑ በሕዝብ ላይ ጉዳት፣ በደል እና ግፍ መፈጸሙን ተናግረዋል። ውይይቱ የመንግሥት ሠራተኞች እየተከናወነ ያለውን የጸጥታ እና የልማት ሥራ በተገቢው ተረድተው መንግሥትን እንዲደግፍ ፋርዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ጽንፈኛው ሕዝብ ለችግር መዳረጉን ያነሱት ኀላፊው ኀብረተሰቡ ይህንን በጽናት ሊያወግዘው ይገባል ነው ያሉት።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ጊዜው ታከለ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እመልሳለሁ ብሎ ጫካ የገባው ኀይል ምን እየሠራ እንደኾነ እውነቱ መውጣቱን ተናግረዋል።

ውይይቱ የመንግሥት ሠራተኞች የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ወደ አስተማማኝ ሰላም ለመለወጥ የበኩላቸውን እንዲጫወቱ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“አሚኮን መለወጥ እና ማሻሻል ክልሉን በሁለንተናዊ መንገድ ማሻሻል ነው” አቶ ዛዲግ አብርሃ
Next article“ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)