3ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነት እና የልማት ጉባኤ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው።

24

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት 3ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነት እና የልማት ጉባኤ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ግንቦት 05 እና 06/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊካሄድ መኾኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት መግለጫ ጉባኤው አፍሪካ የኮንፈረንስ ማዕከል እንድትኾን ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

ጉባኤው በ2063 የአፍሪካን የልማት አጀንዳዎችን ለማሳካትም የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያስችላል ነው ያሉት።

እንደ ጠቅላይ ጸሐፊው ገለጻ ከኮንፈረንሱ የሚገኙ ውጤቶች ተለይተው በአፍሪካ ኅብረት እና የቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲቀርቡ እና ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶች፣ ለልማት እና ማኅበራዊ ጉዳዮች በመነሻ ግብዓትነት ይቀርባሉ ተብሏል።

ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ከ80 በላይ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የሀገር በቀል ዕውቀት እና የባሕል መሪዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ተመራማሪዎች በኮንፈረንሱ እንደሚታደሙ ተገልጿል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ረሕመት አደም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት
Next articleየአሠሪ እና ሠራተኛ መብት እና ግዴታ እስከ ምን ድረስ ነው?