“የዘር አቅርቦት ችግር አይኖርም”

10

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለምርት እና ምርታማነት መጨመር የምርጥ ዘር ግብዓት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮም በምርት ዘመኑ በሁሉም የሰብል ዓይነቶች 292 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለመሠብሠብ አቅዶ አየሠራ መኾኑን የቢሮው ምክትል ኀላፊ አጀበ ስንሻው ተናግረዋል።

እስካሁንም 267 ሺህ 652 ኩንታል ምርጥ ዘር መሠብሠብ መቻሉን አቶ አጀበ ተናግረዋል፡፡ የምርጥ ዘር ማሠባሠብ ሂደቱ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በበጀት ዓመቱ የዘር አቅርቦት ችግር ሊከሰት አይችልም ብለዋል፡፡ በክልሉ በስፋት አርሶ አደሩ የሚፈልገው የምርጥ ዘር አይነት የበቆሎ ዘር እንደኾነ ያነሱት ምክትል ቢሮ ኀላፊው እስካሁን ባለው ከ180ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር መሠብሠቡንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት እንደ እጥረት የሚያነሳው የውጭ የበቆሎ ዝርያዎች ምርጥ ዘር ነበር ያሉት አቶ አጀበ አሁን እሱን ሊተኩ የሚችሉ እና አካባቢውን የሚመጥኑ የበቆሎ ምርጥ ዘር አይነቶች በበቂ ኹኔታ መኖራቸውን ተናግረዋል። የምርጥ ዘር ማሠባሠብ ሂደቱ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በበጀት ዓመቱ የዘር አቅርቦት ችግር ሊከሰት አይችልም ነው ያሉት፡፡

በክልሉ በስፋት አርሶ አደሩ የሚፈልገው የምርጥ ዘር አይነት የበቆሎ ዘር እንደኾነ ያነሱት ምክትል ቢሮ ኀላፊው እስካሁን ባለው ከ180 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር መሠብሠቡንም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት እንደ እጥረት የሚያነሳው የውጭ የበቆሎ ዝርያዎች ምርጥ ዘር ነበር ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው እሱን ሊተኩ የሚችሉ እና አካባቢውን የሚመጥኑ የበቆሎ ምርጥ ዘር አይነቶች በበቂ ኹኔታ መኖራቸውን ተናግረዋል።

አቶ አጀበ የምርጥ ዘር ጥራትን ለማስጠበቅ የግብርና ተቋሙ በአመራረት እና በብዜት ላይ የሚያደርገው ክትትል እንዳለ ኾኖ የግብርና ደኅንነት እና ባለሥልጣን ጥራቱ ምን ያህል የተጠበቀ ነው የሚለውን በላብቶሪ ፍተሻ ያደርጋል ብለዋል፡፡ እያንዳንዱ ምርጥ ዘር በላብራቶሪ ተፈትሾ የብቅለት መጠኑ የተሟላ ሲኾን ለዘር ስርጭት የሚቀርብ ይኾናል ነው ያሉት፡፡

በዚህ መንገድ 150ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዘር ተፈትሾ ጥራቱ የተረጋገጠ በመኾኑ ለስርጭት እንደቀረበም አስገንዝበዋል፡፡ እንደ አቶ አጀበ ገለጻ እስካሁን ባለው ሂደትም 13ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡ ምርጥ ዘርን ለማባዛት መነሻ ወይም እናት ዘር ያስፈልጋል፤ ይህንን መነሻ ወይም እናት ዘር በመመርመር፣ በመፈተሽ እና በማላመድ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩቱ እየሠራ ያለው ሥራ አስተዋጽኦው የጎላ እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የአባቶቻችንን የቅርስ ሥራ ጥበብ ከአሁኑ ትውልድ ጋር የሚያስተሳስር የኖራ ፋብሪካ ልንተክል ነው” የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ
Next article“መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት