“መርሐችን የጀመርነውን የልማት ሥራ አጠናቅቀን ሪቫን መቁረጥ ነው” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

14

ወልድያ፡ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረደ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ የቢሮ ግምባታን አስጀምሯል። የጉባላፍቶ ወረዳ አሥተዳዳሪ ሀብታሙ በየነ ሕንጻው ባለ ስምንት ወለል ሲኾን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል ብለዋል። ወጭውም በወረዳው በጀት እና በኅርተሰቡ ተሳትፎ አንደሚሸፈን ነው የገለጹት።

ግንባታው በሦስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ሕንጻው ኅብረተሰቡን በአንድ ማዕከል ለማገልገል ፋይዳው ጉልህ በመኾኑ ሥራው በትብብር ሊጠናቀቅ አንደሚገባ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እንዲህ አይነት ግንባታዎች ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ማዕከል በመሠብሠብ በተቀላጠፈ እና በስኬት ለማሳለጥ ብሎም አገልግሎትን በአንድ መሶብ ለማቅረብ ያለሙ ናቸው ብለዋል።

ይህም ግልጽነት እና ሁለንተናዊ አገልግሎት አሰጣጥን ያቀላጥፋል ነው ያሉት። ግንባታዎች በጥራት እና ከባሕል ጋር ተሰናስለው ከተሠሩ ለከተማ ውበት እና ማራኪ መኾን ብሎም ለቱሪዝም ማደግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ነው ያብራሩት።

ይሁን እንጂ ሕንጻውን ጀመርን ማለት ጨረስን ማለት አይደለም ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ መርሐችን የጀመርነውን የልማት ሥራ አጠናቅቀን ሪቫን መቁረጥ ነው ብለዋል።

ስለዚህ የገባነውን ቃል እና የጀመርነውን ግንባታ ፈጽመን የምናሳይ መኾን አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሠማራት ተጠቃሚ መኾናቸውን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ወጣቶች ተናገሩ።
Next article“የአባቶቻችንን የቅርስ ሥራ ጥበብ ከአሁኑ ትውልድ ጋር የሚያስተሳስር የኖራ ፋብሪካ ልንተክል ነው” የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ