የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ እየተሠራ ያለውን የኮሪደር ልማት ጎበኙ።

37

ደሴ፡ ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ801ኛ ኮር አባላት በደሴ ከተማ እየተሠራ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል።

የሠራዊት አባላቱ የልማት ሥራዎች በፍጥነት እና በጥራት እየተከናወኑ መኾኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ልማቶች የሚከናወኑት ሰላም ሲኖር በመኾኑ የአካባቢው ማኅበረሰብ ሰላም ወዳድነቱን አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል ብለዋል።

በጉብኝቱ የተገኙት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም በመኖሩ ያለ ስጋት የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደኾነ አስረድተዋል።

የጸጥታ ኀይሉ ሀገርን ለመጠበቅ መስዋትነት እየከፈለ መኾኑን ያነሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የልማት ሥራዎቻችን ሁሉ በተያዘላቸው መርሐግብር እንዲጠናቀቁ እያበረከተ ያለው ሚናም የላቀ ነው ብለዋል።

በጉብኝቱ ላይ የ801ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌን ጨምሮ ሌሎችም የሠራዊቱ አባላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገነቡ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።
Next articleባሕር ዳርን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።