ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገነቡ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።

56

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋዬ እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገነቡ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።

መሪዎቹ ከተመለከቷቸው ሥራዎች መካከል የአጼ ፋሲል አብያተ መንግሥታት እድሳት፣ የከተማዋ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት፣ የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የአንድ ማዕከል የገበያ ቦታ ግንባታ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

አይራ በመባል በሚታወቀው አካባቢ የሚገነባውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ለጎንደር ውበት የራሱ ፋይዳ ያለው እንደኾነ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ በ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት የሚገነባ ነው። ግንባታው ሲጠናቀቅ የከተማውን ፍሳሽ ቆሻሻ በማጣራት ውኃውን ለመስኖ፤ ቀሪውን ደግሞ ለአፈር ማዳበሪነት የሚያውል ነው ተብሏል።

የግንባታው ሥራ አሁን ላይ 70 በመቶ መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። በዚሁ በአይራ አካባቢ የሚሠራው የአንድ ማዕከል የግብይት ቦታም የኑሮ ውድነትን ከማቃለል አኳያ ለጎንደር ከተማ እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው።

አምራቾች እና ሸማቾች በቀጥታ የሚገናኙበት በመኾኑ የአካባቢው አርሶ አደሮችም ምርታቸውን ያለገበያ ችግር ለመሸጥ ያስችላቸዋል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሰላም እና የልማት ተጠቃሚው፤ የጦርነትም ቀዳሚ ተጎጅው ሕዝብ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleየሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ እየተሠራ ያለውን የኮሪደር ልማት ጎበኙ።