ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመገጭ መሥኖ ግድብ ፕሮጀክት ተገኝተው የሥራውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።

30

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የአማራ ክልል እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር መሪዎች በመገጭ መሥኖ ግድብ ተገኝተው የፕሮጀክቱን የግንባታ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው። መገጭ የመስኖ ግድብ ከተጀመረ በርካታ ዓመታት ቢኾነውም ሳይጠናቀቅ ቆይቷል።

አሁን ላይ ግን ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ በተሰጠው ልዩ የሥራ አቅጣጫ መሠረት በፍጥነት እየተሠራ ነው።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን አርሶ አደሮች የመስኖ ልማት ተጠቃሚ እና ትርፍ አምራች ከማድረግም ባለፈ የጎንደር ከተማን የቆየ የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ዛሬም ከፍተኛ መሪዎች በቦታው ተገኝተው የግንባታ እንቅስቃሴውን እየተመለከቱ ሲኾን ሥራውን ለማፋጠን በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ዙሪያም እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleለኮሪደር ልማት የሚተከሉ ስማርት ፖሎችን እያመረተ መኾኑን የአማራ ብረታብረት ኢንዱስትሪ አስታወቀ።
Next article“ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ማጠናከር ለተረጋጋ ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ ነው” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ