“መሪዎች የችግር ወቅት እና የአዲስ ተስፋ አመራር ብቃት ልትሰንቁ ይገባል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

21

ወልድያ: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ከወልድያ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ጋር በሰላም፣ በሕዝብ ግንኙነት፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። የቀጣይ ወራት የሥራ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በጸጥታ ችግር አዙሪት እንድንቆይ ያደረገንን ምክንያት መፈተሽ ያስፈልጋል ብለዋል። የሕዝብን ፍላጎት ተገንዝቦ የአመራር ስልትን ፈጥኖ ማስተካከል ከመሪ የሚጠበቅ ተግባር መኾኑንም አስገንዝበዋል። ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ይህንን መረዳት የሚችል መሪ እና ማኅበረሰብ መገንባት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ሕዝብን የሚያሠባሥብ ትርክትን ገንብተን ሕዝባችንን ማሻገር አለብን ብለዋል። ” መሪዎች የችግር ወቅት እና የአዲስ ተስፋ አመራር ብቃትንም ልትሰንቁ ይገባል” ብለዋል።

በአዲሰ ዘመን የሚያስፈልገውን እና ያገኘናቸውን ስኬቶች በልኩ መመዘን፣ ሌላ አዲስ ሀሳብ እና በየቀኑ ለሚለዋወጠው የአዲስ ዘመን ባህሪያት በስኬት ውስጥ መዝለቅ የሚያስችል የአመራር ቁመና መገንባት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ይህንን ለማድረግ ብዙ እርሾ አላችሁ፤ በተግባርም መሬት ላይ በልማት እያሳያችሁ ነው ብለዋል። ወልድያ ከተማ የየጁ ስርወ መንግሥት ማዕከል እንደመኾኗ የሥነ መንግሥትን ሥርዓት ያዳበረ ሕዝብ ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ መሪዎችም በአባቶቻቸው ሥነልቦና ልክ የታነጹ ሊኾኑ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ፋይዳ ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው።
Next articleየሲራራ ንግድ ባለታሪኳ ጎንደር ዛሬም በዘመናዊ ንግድ ደምቃለች።