“ፋይዳ ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው።

32

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሩጫ ውድድር ሊካሄድ ነው።

ውድድሩ በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ እና ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል። ሩጫው “ፋይዳ ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት ግንቦት 3/2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

“ፋይዳ ለኢትዮጵያ” በሀገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግብን ለማሳካት እየተሠራ መኾኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ ኀይለሥላሴ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

ምዝገባ ከተጀመረበት ጊዜ እስካሁን ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ ያለውን የኅብረተሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ በትብብር እንደሚሠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ በላይ ደጀን ተናግረዋል። ግንቦት 3/2017 ዓ.ም በሚካሄደው የሩጫ ውድድርም አትሌቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳታፋሉ።

በሁለቱም ጾታ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የሚወጡ ሯጮች የገንዘብ እና የሜዳሊያ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ራሔል ደምሰው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next article“መሪዎች የችግር ወቅት እና የአዲስ ተስፋ አመራር ብቃት ልትሰንቁ ይገባል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)