ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን ጎበኙ።

22

ጎንደር: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስቻለ አላምሬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መስፍን አበጀ (ዶ.ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ሙሉ ወጪው በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሚሸፈን ነው። ማዕከሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቅቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ልዩ አቅጣጫ ተቀምጦለት እየተሠራ መኾኑ ተመላክቷል።

የምገባ ማዕከሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ ነው።

ግንባታው አሁን ላይ መጠናቀቁም ተገልጿል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አገልግሎት እንደሚገባም ተጠቁሟል። ማዕከሉ እንደሀገር የተያዘውን ሰው ተኮር የልማት ግብ ማሳያ መኾኑንም ተመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየእናቶች በጤና ተቋማት የመውለድ ምጣኔን ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
Next article“በተወሰኑ የቱሪዝም ዘርፎች ላይ የተንጠለጠለውን የቱሪዝም አካሄድ በመቀየር አማራጭ ዘርፎችን ማስፋት ተገቢ ነው” የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ