በደቡብ ጎንደር ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።

16

ደብረ ታቦር: ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ በተካሄደው የሽኝት ሥነ ሥርዓት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፣ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ በሪሁን መንግሥቱ፣ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ 303ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተሾመ ይመር እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

የሀገር መካላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ተመልምለው ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶች የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ በርትተው እንደሚሠሩ ገልጸዋል። የሀገር ዘብ የኾነውን መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀላቸውም ደስተኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በሽኝት ፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ በሪሁን መንግሥቱ አባቶቻችን በተጋድሏቸው የሀገራችንን ዳር ድንበር ጠብቀው እንዳስረከቡን ተናግረዋል።

አሁንም እንደ ክር እና ማግ አንድ በመኾን የተረከቡትን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው እንዲያስቀጥሉ ለምልምል አባላቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከራሱ በፊት ሀገሬን የሚል የሀገር ታዛዥ መከላከያ ተቋም ነው ያሉት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ አንድነቷ የጠነከረ ሀገርን አስጠብቆ ለማስቀጠል አደራ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

“የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀላችሁ ወንድሞቻችን የሀገርን ሉዓላዊነት ከፍ ታደርጋላችሁ” ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጎንደር ከተማ አሥተዳደር መሪዎች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለኮሪደር ልማት ሰጡ።
Next article“17 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው