ማኅበረሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክረ ሃሳብ በአግባቡ በመተግበር የወባ ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚገባ ተጠቆመ።

18

ደብረ ማርቆስ: ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምስራቅ ጎጃም ዞን የወባ ተጋላጭ ከኾኑ አካባቢዎች መካከል ተጠቃሽ ነው። በዞኑ በክረምት መግቢያ ላይ ሊከሰት የሚችል የወባ በሽታን ለመከላከል የባለሙያውን አቅም በማሳደግ ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እና አስፈጊ የኾኑ የሕክምና ግብዓቶችን የማሟላት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የዞኑ የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ባለሙያ ንብረት በሪሁን ተናግረዋል።

የወባ በሽታን የቅድመ መከላከል ሥራ ከሌሎች የዘመቻ ሥራዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑንም አስታውቀዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ140 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አቶ ንብረት ገልጸዋል።

ቆላማ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የኾነ የወባ ስርጭት ይስተዋላል ያሉት ባለሙያው በእነዚህ ቦታዎች ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክረ ሐሳብ በአግባቡ በመተግበር የወባ ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚጠበቅበትም ባለሙያው አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ።
Next articleየአሁኑ ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ ተጠቅሞ ሰላሙን በማስጠበቅ በልማቱ ሀገሩን ከፍ አድርጎ ማሳየት ይገባዋል።