
ደብረ ማርቆስ: ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር “የጥፋት እጆችና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት በከተማዋ ከሚገኙ ሴቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መንግሥት ችግሮችን ለይቶ ሊፈታ ይገባል ብለዋል። በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኾነው ችግር የሚፈጥሩ አካላትንም ለይቶ የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የክልሉ ሕዝብ በነጻነት ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብቱን ከመጠበቅ በተጨማሪ የክልሉ ሕዝብ በየጊዜው የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መፍታት እንደሚገባው አንስተዋል፡፡ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሴቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላችሁ ጠቁመዋል። ለዚህም በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
መንግሥት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ መልካሙ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ኀይሎችን ወደ ሰላማዊ ሕይዎት እንዲመጡ እያደረገ ስለመኾኑ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን