
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የሰሜን ጎጃም ዞን አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን እና ሌሎችም መሪዎች ከጎንጅ ቆለላ አዲስዓለም ከተማ እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው። ውይይቱ በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ዙሪያ አተኩሮ ነው እየተካሄደ ያለው።
የውይይቱ ተሳታፊዎች አካባቢው ሙሉ በሙሉ ሰላም እንዲኾን ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኀይሎች ጋር ተናቦ እንደደሚሠራ አንስተዋል።
ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውኃ እና የመንገድ አውታር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። አካባቢው በማዕድን የበለጸገ ቢኾንም ተጠቃሚ አልኾንም፤ በዘርፉ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግሥት በትኩረት ሊሠራ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን