
ወልድያ: ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የውላ ወንዝ ተፋሰስ ልማትን ጎብኝተዋል።
ውላ ወንዝ የክረምት ወቅት ጎርፍ የውርጌሳ ከተማ ነዋሪዎችን እና አርሶ አደሮችን እያማረረ መኾኑን የውርጌሳ ከተማ ነዋሪዎች አስረድተዋል።
ከአሁን በፊት በከባድ ማሽን የጎርፉ አሸዋ እየተነሳ ስጋቱ እንዲቀንስ ይደረግ ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ በጸጥታ ችግር ምክንያት ማሽን ገብቶ ሊያፀዳ ባለመቻሉ ሕዝቡ መቸገሩን ነው የገለጹት።
ይሁን እንጂ አሁን ላይ በሴፍቲኔት ልማት እየተሠራ ያለው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ተስፋ እንደሰጣቸው አስረድተዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ኤክስካቫተር ማሽን ገብቶ ደለል እንዲያፀዳ ከወረዳው ጋር እንነጋገራለን ብለዋል። የተፋሰሱ ልማት እንዲጠናቀቅ የአካባቢያችሁን ጸጥታ ልትጠብቁ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን