በግሪክ ማላካሳ የስደተኞች ካምፕ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ደቅኗል፡፡

221

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 12/2012 ዓ.ም (አብመድ) አፍጋኒስታናዊው ጋዜጠኛ ሬዛ በሺዎች ከሚቆጠሩና በግሪክ አቴንስ አቅራቢያ ማላሳካ ከተጠለሉ ስደተኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ለቢቢሲ በሰጠው መረጃ ለስደተኞቹ በቤት ውስጥ መቆየት በቫይረሱ ከመያዝ አላስጣላቸውም፡፡ ሬዛ ለሁለት ወራት አደረኩት ባለው ምርመራ ወረርሽኙ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሰደድ እሳት ስጋት ፈጥሯል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው ለ14 ቀናት የእንቅስቃሴ እገዳ ተጥሏል፡፡ ማንም ሰው ከመጠለያው ጣቢያው መውጣትም መግባትም አይችልም፡፡ ነገር ግን በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ስደተኞቹ ተጋላጭነት ከፍ እንደሚል ምልከታውን አጋርቷል፡፡ በአብነት ምንም እንኳን በቫይረሱ እንደተያዘ የታወቀ ቢሆንም ከቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ጋር በአንድ ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ የሚኖር ግለሰብን በመጥቀስ፡፡ ክፍሉ የእጅም ሆነ የገላ መታጠቢያ የለውም፡፡ ከጎረቤት ጋር ነው የሚጋሩት፡፡ ይህ ደግሞ የስደተኞቹን ለወረርሽኙ ተጋላጭነትን ጨምሮታል፡፡ ለመደበኛ አገልግሎት መጠለያ ጣቢያው ውስጥ ወዳለው የሕክምና ማዕከል የሚመጡ ስደተኞችም በቫይረሱ ስላለመያዛቸው እርግጠኛ አይደሉም፡፡ በቫይረሱ ተይዘው ዕርዳታ የሚደረግላቸው ስደተኞች ጋር ያለው ንክኪም ሌላው ስጋት ነው፡፡

በግሪክ የስደተኞች ሚኒስትር ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው እና ጉዳዩን እንደሚያጣሩት ገልጸዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በበኩሉ ለግሪክ መንግሥት ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በመጠለያ ጣቢያው 20 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሉ፡፡ የግሪክ መንግሥት ደግሞ በስደተኞች መጠለያ የቫይረሱ የስርጭት መጠን 0 ነጥብ 2 በመቶ እንደሆነና እና የተመዘገበ ሞት አለመኖሩን ገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

በየማነብርሃን ጌታቸው

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየዓለም ባንክ ለኬንያ የአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleህንድና ባንግላዴሽ በከባድ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ስጋት ላይ ወድቀዋል፡፡