
ባሕር ዳር: ሚያዚያ: 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 84ኛው የአርበኞች ድል በዓል ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። በድል ሃውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትም እየተተከናወነ ነው።
ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በተጨማሪ በድል ሃውልት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን በመወከል ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን፣ የጀግኖች አርበኞች ማኅበርን በመወከል ደግሞ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን እንዲሁም የአዲስ አበባ ባሕል አና ኪነ-ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ.ር) የአበባ ጉንጉን በሐውልቱ ስር አስቀምጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!