ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጋሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ሥራን አስጀመሩ።

28

ወልድያ: ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጋሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ሥራን አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱረህማን፣ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የጋሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ የአስፋልት መንገድ የረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ ቆይቷል። ታሪካዊቷን እና የቱሪዝም መዳረሻ የኾነችውን ላሊበላን አቋርጦ የሚሄደው መንገዱ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

የቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ፕሮጄክቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተመላክቷል። ለፕሮጄክቱ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleለትምህርት ዘርፉ መፍትሄ ማበጀትን ዓላማው ያደረገ ውይይት በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄደ።
Next articleበጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተሠሩ የሚገኙ የጥናት እና ምርምር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቆመ።