
በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ “የጥፋት እጆችና መዘዞቹ” በሚል መሪ ሀሳብ ከወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኅላፊ እንድሪስ አብዱ የሀገር ሰላም፣ ልማት እና ብልጽግና ሰፊውን ድርሻ የሚወስደው የተማረው የሰው ሀይል በመኾኑ የመንግሥት ሠራተኛው ሰላምን ለማጽናት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ኅላፊነት ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
በውይይቱ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንድሪስ አብዱ፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመርን ጨምሮ የየደረጃው የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ተገኝተዋል።