
ሰቆጣ: ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱረህማን፣ የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)፣ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥተዳዳሪ ኀይሉ ግርማይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በሰቆጣ ወረዳ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የአሏቅ የዶሮ ማስፈልፈያ ማዕከልን ጎብኝተዋል። ግንባታውን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገውም ተመላክቷል።
በሰቆጣ ወረዳ በወለህ እየተገነባ የሚገኘውን ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታንም ጎብኝተዋል። ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ በጥራት እና በፍጥነት እየተገነባ መኾኑም ተገልጿል።
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ሲጠናቀቅ 600 ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም እንዳለው እና ደረጃቸውን የጠበቁ ሕንጻዎች እንደሚኖሩትም ተመላክቷል።
በ16 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ በ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እየተገነባ እንደሚገኝም ነው የተብራራው።
የትምህርት ቤቱን ሥራ በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ የግብዓት አቅርቦት በፍጥነት እንዲገባላቸውም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን