
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች ተገኝተው ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በሰላም እና በልማት ሥራዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎችም የክልል እና የዞኑ መሪዎች ተገኝተዋል።
መሪዎች በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ከሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ነው እየተወያዩ ያሉት። የጭንጫየ፣ ባሕሬ ግንብ እና ምንዝሮ የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።
ውይይቱ የጎንደር እና የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በመመለስ በሙሉ አቅም ወደ ልማት ለመግባት የሚያስችል ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን