
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን ከአዴት ከተማ አሥተዳደር እና የይልማና ዴንሳ ወረዳ ነዋሪዎች ”የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የርእሰ መሥተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ፣ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን፣ የመከላከያ ሠራዊት በምሥራቅ ዕዝ የ304ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዲሱ ሙሐመድ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
በውይይቱ ኅብረተሰቡ ለሰላም እንዲረባረብ እና ችግሮች በውይይት ተፈተው ወደተሟላ ሰላም ስለሚገባበት ሁኔታ እንደሚመከር ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን