
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 460 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አራት (24) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ (389) ደርሷል፡፡
ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 12 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፣ ስምንቱ በቫይረሱ ከተያዙ ጋር ንክኪ የነበራቸው፣ አራቱ ደግሞ የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክም በቫይረሱ ከተያዙ ጋርም ንክኪ የሌላቸው እንደሆኑ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
ዘጠኙ ከአዲስ አበባ (አምስት በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ያላቸው፣ አራት የውጭ ሀገራት ጉዞም ሆነ በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ የሌላቸው)፣ ስምንቱ ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸውና ከመተማ ለይቶ ማቆያ የነበሩ)፣ ሰባቱ ደግሞ ከትግራይ ክልል (አራት የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ ሶስት በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ያላቸው ከእነዚህ ውስጥ አንድ ከመቀሌ ለይቶ ማቆያ፣ ስድስቱ ከማይካድራ ለይቶ ማቆያ የነበሩ) መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።