አሠሪ ተቋማት ለጸደቁ ደንቦች እና መመሪያዎች ዕውቅና በመስጠት ገቢራዊ ማድረግ አለባቸው።

17

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዘንድሮው የሠራተኞች ቀን በዓለም ለ136ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ ይከበራል።

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኀበራት ኮንፌዴሬሽን የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የኢንዱስትሪ ግንኙነት ኀላፊ አዜብ ማርቆስ ቀኑ ሲከበር ሠራተኞች ስለመብቶቻቸው፣ ጥቅሞቻቸው እና ፍላጎታቸው ድምጽ በመኾን ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር እና እንደ ክልል ሠራተኛው በኑሮ ጫና ውስጥ ስለሚገኝ እና ከዋጋ ግሽበት አኳያ የደመወዝ የገቢ ግብር ምጣኔ እንዲሻሻል፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ጥያቄ መቅረቡን ኀላፊዋ አንስተዋል።

የሠራተኞች ደህንነት እና ጤንነት እንዲጠበቅም ኮንፌዴሬሽኑ እየሠራ ነው ብለዋል።

አሠሪ ተቋማት ለጸደቁ ደንቦች እና መመሪያዎች ዕውቅና በመስጠት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ኀላፊዋ አሳስበዋል።

የሠራተኞች ኮንፌደሬሽን እንደ ሀገር የሠራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል እና ጥያቄዎችን ምላሽ ለማሰጠት ከሚመለከታቸው ጋር በቅርበት እየተነጋገሩበት ይገኛሉ ነው ያሉት። መፍትሔ ይገኛልም ብለው ተስፋ ማሳደራቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል።

የዓለም የሠራተኞች ቀን በዓለም ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ ይከቀራል።

ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

Previous articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት በ44ኛ መደበኛ ስብሰባው በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
Next articleየአሲዳማ አፈር የግብርናው ዘርፍ ፈተና ኾኗል።