ለሀገሪቱ ልማት አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለው ሠራተኛ በኢኮኖሚውም በፍትሐዊነት መንገድ ተጠቃሚ ሊኾን ይገባል።

16

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ እንደ ክልል ደግሞ ለ24ኛ ጊዜ በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኀበራት ኮንፌዴሬሽን የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አጉማስ ዳኘው በአንዳንድ የሥራ መሪዎች እና አሠሪዎች ከሚፈጸምብን የመብት ንፍገት፣ በደሎች እና ከፍትሕ ሂደት መጓተት በላቀ ደረጃ ተጭኖን ያለው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ እየተባባሰ መጥቷል” ብለዋል።

በኢንዱስትሪዎች ውስጥ እየሠሩ ያሉት ሠራተኞች ደመወዝ ዝቅተኛ ነው፤ በሠራተኛው ደመወዝ ላይ ያለ አግባብ ጫና እያሳደረ ያለው የሥራ ግብር ምጣኔ ሊሻሻል ይገባዋል ነው ያሉት።

ለሀገሪቱ ልማት አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለው ሠራተኛ በኢኮኖሚውም በፍትሐዊ መንገድ ተጠቃሚ እንዲኾን መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች አስቸኳይ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል ።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ፈጠራ እና ፍጥነት የታከለበት የክህሎት ግንባታ ቀጣይነት ላለው የሥራ እድል ፈጠራ ወሳኝ ነው” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
Next articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት በ44ኛ መደበኛ ስብሰባው በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።