በሙያቸው አስተዋጽኦ ለማድረግ ሰላም እንደሚያስፈልግ የባንጃ ወረዳ መምህራን ተናገሩ።

28

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባንጃ ወረዳ “የጥፋት እጆችና መዘዞቹ “በሚል መሪ መልዕክት ከመምህራን ጋር ውይይት ተካሂዷል። የውይይት መድረኩን የመሩት የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪ እና የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ደጋፊ ግዛቸው ሙሉነህ በክልሉ የተፈጠረው ግጭት ከፍተኛ ጫና ከፈጠራቸው ዘርፎች አንዱ የትምህርት ተቋሙ ነው ብለዋል።

በተፈጠረው የሰላም እጦት የክልሉን ሕዝብ ለተራዘመ ስቃይ የሚዳርግ መኾኑንም ገልጸዋል። መምህራን ለሰላም መስፈን አበርክቷቸው የጎላ መኾኑን የተናገሩት አቶ ግዛቸው በቀጣይ ዓመት በሁሉም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አከባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። የተፈጠረው የሰላም እጦት ለማስተካከል መምህራን የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል ።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው መምህራን ትውልድን በማነፅ እና ግብረ ገባዊ ስብዕናን በማላበስ የዜግነት ኀላፊነት አለባቸው ነው ያሉት። መምህራን በመኖሪያ እና በሥራ አከባቢ ለሌሎች አርዓያ ሆኖ መገኘት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። በ2018 የትምህርት ዘመን የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ለማስከፈት ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊ መምህራንም የምንወደውን የመምህረነት ሙያችንን ለመቀጠል ሰላም ያስፈልጋል ብለዋል። በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት መነፈግ ዜጎችን በሀገራቸው ባይተዋር እንዲሆኑ እያደረገ መኾኑን ነው የተናገሩት። ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው መንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ መሆን መቻል አለበት ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጸጥታ ችግሮችን ለመሻገር ያለመ ውይይት በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ።
Next articleየታጠቁ ኃይሎች ለሰላም ዝግጁ እንዲኾኑ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡