የጸጥታ ችግሮችን ለመሻገር ያለመ ውይይት በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ።

8

ደብረ ታቦር: ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ!” በሚል መሪ መልዕክት በቀበሌ ደረጃ ሕዝባዊ ውይይት በደብረ ታቦር ከተማ ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ታጥቆ ጫካ የሚገኘው ሀይል በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሰው ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት በፊልም ታይቷል።

ውይይቱ ሕዝቡ እውነታውን እንዲያውቅ እና በቀጣይ ችግሮችን ለመሻገር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

በውይይት መድረኩ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን፣ የአማራ ሥራ አመራር አካዳሚ ኀላፊ እሱባለው መሰለ፣ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጸጥታ ኀይሎች የሕዝብ ደጀንነታቸውን በተግባር እያረጋገጡ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበሙያቸው አስተዋጽኦ ለማድረግ ሰላም እንደሚያስፈልግ የባንጃ ወረዳ መምህራን ተናገሩ።