የጸጥታ ኀይሎች የሕዝብ ደጀንነታቸውን በተግባር እያረጋገጡ መኾኑ ተገለጸ።

19

ወልድያ: ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት በወልድያ ከተማ አሥተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች ከተመደቡ ሰላም አስከባሪ የጸጥታ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል። በጥፋት ኀይሎች የተፈፀሙ ግፍ እና በደሎች ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በውይይቱ አስተያየት የሰጡ የጸጥታ አባላት በማኅበረሰባችን፣ በራሳችን እና በቤተሰቦቻችን የደረሰዉ ግፍ ከተገለጸው በላይ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኀይሎችን ለመፋለም ሁልጊዜም ዝግጁ ነን ብለዋል። መሪዎች ኅብረተሰቡን የማወያየት ሥራ እንዲሠሩም ጠይቀዋል።

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ደጀኔ ሽባባው ሰላም አስከባሪዎች የሕዝብ ደጀንነታቸውን በተግባር እያስመሰከሩ መኾናቸውን አስረድተዋል።

የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከቀድሞው በላቀ ትጋት መሥራት ያሻል ነው ያሉት። በሚሰማሩበት ግዳጅ ሁሉ ተልዕኳቸውን በድል እንዲወጡ አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዘር አቅርቦት ችግር አይኖርም”
Next articleየጸጥታ ችግሮችን ለመሻገር ያለመ ውይይት በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ።