
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ በውይይት መድረኩ ጽንፈኛው ቡድን በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ያደረሰው ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት አስከፊነት ላይ ጥልቅ ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።
ከእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ኮምዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሰላም ውይይቱ የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
