የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከብራዚል እና ሩስያ አቻቸው ጋር ተወያዩ።

15

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) በብራዚል ሪዮ ዴ ጃኔይሮ እየተካሄደ ካለው የብሪክስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከብራዚል እና ሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቬራ ጋር ባደረጉት ውይይት ብራዚል በብሪክስ የወቅቱ ፕሬዝዳንትነቷ የጀመረችውን ሥራ በማድነቅ ኢትዮጵያ ብራዚል ላስቀመጠቻቸው የብሪክስ የትኩረት አቅጣጫ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

ሚኒስትሮቹ በግብርና ማምረቻ፣በዓለም አቀፍ ተቋማት አሥተዳደራዊ ማሻሻያዎች፣በኢነርጂ ሽግግር እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።ሁለቱ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ እና ብራዚልን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከርም ተስማምተዋል።

ከሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን መርሕ ባደረገ መልኩ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ተጨባጭ በሆኑ የትብብር መስኮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መኾኗን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየገቢ አሠባሠቡን ለማዘመን እየተሠራ ነው።
Next articleየጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል እና አገልግሎቱን ለማሳለጥ እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።